|

“የባህሪ ክኒን ኢየሱስ ነው እርሱ የገባበት ችግር የለበትም። ከቅባት አገልጋይ የባህሪ አገልጋይ ይበልጣል። የቅባት
አገልጋይ እንደ ሳምሶን አይነት
ነው። እዚጋ ፐ ብላችሁት እዛጋ ከደሊላ ጋር ይገኛል። ምነካው ትላለህ። ፍልስጥኤምን ድራሹን አጥፍቶ በሚደነቅ ሃይል እዚጋም በደሊላ ያስደንቅሃል በሁለቱም ነው የሚያስደንቅህ”
--------------------
“መፈታት ማለት እንደፈለጉ መሆን አይደለም እንደፈለጉ አለመሆን እንጂ”
----------------------
“አዲስ የሆነ መገለጥን (መረዳትን)
ለመቀበል ዝግጁ ካልሆንክ የሕይወትህን ለውጥ ማምጧት
የማትችል ትሆናለህ።” (ሐዋ 17፡19-20፣ 32-34)
-------------------
“የእግዚአብሔር ሃይል በማይገኝበት ስፍራ ሰዎች በሃሳቦች መካከል ሲያነክሱ ይገኛሉ።”
------------------
“ከእርሱ ከሚቀበለው በረከት በላይ እግዚአብሔርን የሚወድ
ሰው የበረከትን ብዛት ሁሉ ትቶ እግዚአብሔርን እንዲከተል ያደርገዋል እንጂ ጌታን አያስረሳውም።”
ፓስተር ሚካኤል ወንድሙ (ሚኪ)
|